ሥራ አጣን ወይስ ስራው አጣን ? በፍቅርተ ተሾመ ሜሮን አልጋዋ ላይ ተኝታለች፡፡ እንደ ወትሮዋ ሁሉ ሌሊቱን ሙሉ ፊልም ስታይ አድራ ቀትር ላይ ነው የነቃችው፡፡ ከመንቃቷ ሀሳቦች ሁሉ እኔ ልቅደም ይሸቀዳደማል፡፡ ቤተሰቦቼ ምን ያስቡ ይሆን፣ እኔስ ግን መቼ ነው ሁሌ አንድ አይነት የሚሰለች ኑሮ የምኖረው፣ ቤተሰቦቼ አርጅተዋል ይሄ ሁሉ ለፍተውብኝ ሳልክሳቸው ጊዜው ሄደኮ እያለች ታብሰነስናለች፡፡ አንድ ግለሰብ በህይወት ሂደቱ ውስጥ ቤተሰብ፣ ጎረቤቶቹ እና በትምህርት ቤት አካባቢ ያሉ ሰዎች ማንነቱ ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ ኖሯቸው ይገነቡታል ደግሞም በተዘዋዋሪ ሲወለድ ካዋለደው/ችው ነርስ ወይ ዶክተር አንስቶ የልደት ካርዱን አትሞ፣ ፈርሞ እስከሚሰጠው ሰው ድረስ የህይወቱን ማይክሮ ሰከንዶችም ቢሆን ጊዜ ይወስዳሉ ተፅዕኖም ይኖራቸዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ በዚህም የአንዳችን ከአንዳችን ጋር ያለንን ባህላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ትስስር መፍታት እና መበተን አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ሂደት ሰው እያደገ ከልጅነት ወደ ወጣትነት ይደርሳል የተሰጠውን ለመስጠት ደግሞ በድጋሚ ለመቀበልም ዝግጅት ወደ ማድረግ ይደርሳል፡፡ በተፈጥሮም ጉልበት፣ ሃይል፣ ፍጥነት፣ ክህሎትን በሰፊው እንድንጠቀምበትና እንድንጠቅምበት ሜዳው ሰፊ ይሆናል፡፡ በሀገራችን 43% የሚሆነውን የህዝብ ቁጥር ድርሻ የሚወስዱት ወጣቶች ናቸው፡፡ እንደ አንድ ሀገር ሀብትነት ደግሞ የሀገሪቷ ምጣኔ ሀብት አንቀሳቃሽ መሆናቸውም የታመነ ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ደግመሞ ሀገሪቷ ውስጥ ከሚወስዱት ድርሻ ጋር ተያይዞ ያለባቸውም ሀላፊነት አለ፡፡ ሜሮን በሆቴል እና ቱሪዝም ከኮሌጅ ከተመረቀች አመት ከአራት ወር ሆኗታል፡፡ ስራ ለማግኘት በሰዎች አስፈልጋለች ጋዜጦችን አንዳንዴ ለማየት ትሞክራለች ግን “እኔ የም...
Posts
Showing posts from April, 2017
- Get link
- X
- Other Apps

ቡሔ ሲነሳ በፍቅርተ ተሾመ ‹‹ ክፈት በለው በሩን የጌታዬን መጣና ባመቱ ኧረ እንደምንሰነበቱ …›› በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን የሚከበረውን የቡሔ ወይንም ደብረ ታቦር በዓልን ምክንያት በማድረግ በዋዜማው ነሐሴ 12 ቀን 2008 ዓ . ም . አባቶችና እናቶች ያቆዩትን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ ለመዘከር ብሎም ለትውልድ ለማስተላለፍ በማመን በባላገሩ አስጎብኚና መኪና ኪራይ አዘጋጅነት በጣይቱ ሆቴል በተለያዩ ባህላዊና ትውፊታዊ መርሐ ግብሮች ተከብሮ ውሏል፡፡ ባህላዊ ልብሶችን በመልበስ ደበሎውን ደርበው ዱላቸውን ይዘውና ጅራፋቸውን በአንገታቸው ላይ ያነገቡ ታዳጊ ወጣቶች በጅራፍ ጩኸት የታጀበውን የሆያ ሆዬ ጭፈራቸውን ለበዓሉ ድምቀት በሚሰጥ መንገድ አቅርበዋል፡፡ የመድረኩ መሪ አቶ ተሾመ አየለ ስለ መርሐ ግብሩ ሲገልፁ ‹‹ እኛ ኢትዮጵያውያን ልዩ የሆነ የማይሸረሸር የማይደፈር ቱባ የሆነ ባህል አለን፡፡ አሁን ጊዜ ልጆቻችን እየተከተሉ ያሉት የውጪውን ባህል ነውና ባህላችንን ለልጆቻችን ለማስተማር የራሳቸውን እንዲያከብሩ ለማድረግ ቡሔን በተለያየ ጊዜያት በተለያዩ አስተማሪና አዝናኝ ፕሮግራሞች አጅበን እናዘጋጃለን፤ ›› ብለዋል፡፡ አሁን ላይ በከተሞች አካባቢ ልጆች ቡሔን መለመኛ አድርገውታል፤ የራሱ ሥርዓት አለው፤ ልመና አይደለም መሆንም የለበትም፤ የሚሰጠውም ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ከነኮባው ነው፤ ግጥሙም ድንበር የዘለለ ኢትዮጵያዊ ለዛ የሌለው ነው ሲሉ ያስተዋሉትን ገልፀዋል፡፡ ይህንንም ባህል ለማሳሰብ ዕለቱን የ...